ልባዊ ስጦታ ከኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል፡ በኢትዮጵያ የግል ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያው የ TAVI ህክምና በስኬት ተከናወነ
ሆስፒታላችን ኢትዮ ጠቢብ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በግል የህክምና ዘርፍ ለወገኖቻችን የጤና እፎይታ የሰጡ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። ሆስፒታላችን በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ታግዞ በህክምናው ላይ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ተግባራትን አከናውኗል።
በዚህ ዓመት በተከበረው የዓለም የልብ ቀን (ሴፕቴምበር 29, 2025 / መስከረም 19, 2018 ዓ.ም) የኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል የልብ ህክምና ክፍል በኢትዮጵያ የግል ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን Transcatheter Aortic Valve Implantation (TAVI) እና Transcatheter Heart Valve (THV) የመትከል ሂደት በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።
ሆስፒታላችን የልብ ህክምናውን ያደረገላቸው የ67 ዓመቱ አባት የደም ግፊትና የኮሌስትሮል ታማሚ ሲሆኑ፣ ባለፉት ስድስት ወራት ያጋጠማቸው የትንፋሽ ማጠር፣ ድካም እና የደረት ጭንቀት ምልክቶች ወደ ከባድ የልብ ህመም ዳርጓቸው ነበር።
ሆስፒታላችን የዓለም የልብ ቀንን ምክንያት በማድረግ፣ በልብ ህክምና እውቅና እና አንቱታን ባተረፉት ዶ/ር መሐመድ በድሩ መሪነት የ TAVI (Transcatheter Aortic Valve Implantation) የህክምና ሂደት በስኬት ማከናወን ተችሏል።
TAVI ምንድን ነው?
TAVI የአኦርቲክ ቫልቭ በሽታ ላለባቸው ታካሚዎች ህይወትን የሚቀይር፣ ፈጣን የማገገሚያ ጊዜ ያለው፣ አነስተኛ ጠባሳ ብቻ የሚጥል እና የደረት ክፍት ቀዶ ጥገናን የሚያስቀር የህክምና ሂደት ነው። አዲሱ የልብ ቫልቭ በደም ቧንቧ በኩል በካቴተር ተመርቶ በታመመው ቫልቭ ቦታ ላይ ይተከላል።
ለሀገራችን ያለው ፋይዳ
በውጭ ሀገር ከ30,000 እስከ 40,000 የአሜሪካ ዶላር የሚያስወጣውን ይህን ህክምና ሆስፒታላችን ሙሉ ወጪውን በመሸፈን በስኬት በማከናወኑ ኩራት ይሰማዋል። ይህ ታላቅ ስኬት በኢትዮጵያ የግል የጤና አገልግሎት ዘርፍ ለከባድ የልብ ቫልቭ በሽታ ታካሚዎች ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።
ህክምናው በሀገራችን መሰጠቱ ከዚህ ቀደም ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ይወጣ የነበረውን ወጪ በግማሽ የሚቀንስ ሲሆን፣ ከዚያም አልፎ የህክምና ቱሪዝምን በሀገራችን ለማስፋፋት ትልቅ ሚና ይጫወታል።
በኢቢኤስ ቴሌቪዥን እንደተዘገበው
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን (EBS TV) “What’s New” ፕሮግራም መስከረም 20, 2018 ዓ.ም (ሴፕቴምበር 30, 2025) “የተሳካው የልብ ህክምና” በሚል ርዕስ በኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ስለተከናወነው የ TAVI ህክምና ዘግቧል። ሙሉውን ዘገባ ከዚህ በታች ይመልከቱ።
ምንጭ፡ EBS TV – What’s New, 30 September 2025
In English: Ethiopia’s first TAVI at a private hospital
On World Heart Day, 29 September 2025, the cardiology team of Ethio Tebib Hospital in Addis Ababa successfully performed a transcatheter aortic valve implantation (TAVI), the first TAVI carried out at a private hospital in Ethiopia. The procedure, also known as TAVR, replaces a diseased aortic valve through a catheter inserted via a blood vessel. It avoids open-heart surgery, leaves minimal scarring and allows a much faster recovery.
The patient, a 67-year-old man with a history of hypertension and high cholesterol, had suffered six months of worsening shortness of breath, fatigue and chest tightness caused by severe aortic valve disease. The procedure was led by interventional cardiologist Dr. Mohammed Bediru.
Ethio Tebib Hospital covered the full cost of the treatment, a procedure that costs USD 30,000 to 40,000 when sought abroad. Offering TAVI locally cuts the cost to roughly half of what Ethiopian patients previously paid to travel overseas, and marks a milestone for patients with severe heart-valve disease in Ethiopia’s private health sector.
The achievement was reported by EBS TV’s What’s New programme on 30 September 2025 (video above). In August 2026 the same team went on to perform the first TAVI in East Africa to be transmitted live to a cardiology congress.
Learn more about TAVI and interventional cardiology at Ethio Tebib Hospital →
In the news / በመገናኛ ብዙኃን
- EBS TV – What’s New (30 September 2025): “የተሳካው የልብ ህክምና”, TV report on the procedure. Watch on YouTube
- Minber News – ሚንበር ኸበር (30 September 2025): “ኢትዮ ጠቢብ ለግል ሆስፒታሎች የመጀመሪያ የሆነውን የልብ ሕክምና ማስጀመሩን ይፋ አደረገ”, report from the hospital’s press briefing. Read on Telegram
For more information or to book a cardiology consultation, call 9000 or request an appointment online.
More videos: every EBS TV segment about the hospital, patient stories and our doctors’ Amharic health talks are collected on Ethio Tebib on EBS TV and YouTube.




