Generic selectors
Exact matches only
Search in title
Search in content
Post Type Selectors
English

ጠቢብ የመካንነት ሕክምና ማዕከል (IVF)

ልጅ የመውለድ ፍላጎትዎ እውን እንዲሆን አብረንዎት እንቆማለን። ከምርመራ ጀምሮ እስከ IVF ድረስ ያለው ሂደት በአንድ ቦታ ይከናወናል።

መቼ መምጣት አለብን?

ለአንድ ዓመት ያህል ያለ መከላከያ ግንኙነት እያደረጉ እርግዝና ካልተፈጠረ ምርመራ ማድረግ ይመከራል። ሴቲቱ ከ35 ዓመት በላይ ከሆነች ግን ከስድስት ወር በኋላ መምጣት ይሻላል። የወር አበባ መዛባት፣ የማህፀን ቀዶ ሕክምና ታሪክ ወይም ተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ ካለ ቀድሞ መምጣት ተገቢ ነው።

መካንነት የሁለቱም ጾታ ጉዳይ ነው። ከሦስቱ ጥንዶች አንዱ ላይ ችግሩ ከወንዱ በኩል ነው። ስለዚህ ምርመራው ሁለቱንም ማካተት አለበት።

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ምርመራ

  • የሆርሞን ምርመራ
  • የዘር ፈሳሽ ምርመራ (semen analysis)
  • የማህፀንና የእንቁላል ቱቦ ምርመራ
  • አልትራሳውንድ ክትትል

ሕክምና

  • የእንቁላል ማብቀያ መድኃኒቶች
  • IUI — የዘር ፈሳሽ ወደ ማህፀን ማስገባት
  • IVF — በላብራቶሪ ማዳቀል
  • ICSI — አንድ ዘር በቀጥታ ወደ እንቁላል ማስገባት

ተጓዳኝ ሕክምናዎች

  • የማህፀን ፋይብሮይድና ሌሎች ችግሮች ቀዶ ሕክምና
  • በላፓሮስኮፒ የሚደረግ ሕክምና
  • የፅንስ ክትትል ከተሳካ በኋላ

ሂደቱ እንዴት ነው?

  1. የመጀመሪያ ቀጠሮ — ሁለታችሁም ትመጣላችሁ፤ ታሪክ ይወሰዳል፣ ምርመራዎች ይታዘዛሉ።
  2. ምርመራ — የሆርሞን፣ የአልትራሳውንድና የዘር ፈሳሽ ምርመራ ውጤቶች ይገመገማሉ።
  3. የሕክምና ዕቅድ — በውጤቱ መሠረት ከቀላል ሕክምና እስከ IVF ድረስ አማራጮች ይብራራሉ፤ ወጪውም አስቀድሞ ይነገርዎታል።
  4. ሕክምና እና ክትትል — በሕክምናው ወቅት በየደረጃው ክትትል ይደረጋል።
  5. ውጤት — እርግዝና ከተፈጠረ የፅንስ ክትትሉ በሆስፒታላችን ይቀጥላል።

ልብ ሊሉት የሚገባ

የመካንነት ሕክምና ጊዜና ትዕግስት ይጠይቃል፤ በመጀመሪያ ሙከራ ሁልጊዜ ውጤት ላይሰጥ ይችላል። ማንኛውም ሆስፒታል እርግዝና እናረጋግጣለን ቢል ማመን የለብዎትም። እኛ የምናደርገው በውጤትዎ ላይ ተመስርተን ትክክለኛውን አማራጭ ማሳየትና በግልጽ መነጋገር ነው።

ቀጠሮ ለመያዝ

9000 ይደውሉ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከላችን +251 935 402 078። ሁለታችሁም አብራችሁ ብትመጡ ይመረጣል።