Generic selectors
Exact matches only
Search in title
Search in content
Post Type Selectors
English

ሐኪም ይፈልጉ

ከ170 በላይ ሐኪሞች — አጠቃላይ ሐኪሞች፣ ስፔሻሊስቶችና ሰብ-ስፔሻሊስቶች — ከ30 በላይ በሆኑ የሕክምና ዘርፎች ውስጥ ይሰራሉ። በስም ወይም በሙያ ፈልገው በቀጥታ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ።

በየትኛው ክፍል ሐኪም ይፈልጋሉ?

የልብ ሕክምና

ካርዲዮሎጂስቶች፣ የልብና ደረት ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስቶችና የህፃናት ልብ ሰብ-ስፔሻሊስቶች። ተጨማሪ

የውስጥ ደዌ

የኩላሊት፣ የሳንባ፣ የሆርሞን፣ የጨጓራና አንጀት፣ የደምና የተላላፊ በሽታ ሰብ-ስፔሻሊስቶች።

የፅንስና ማህፀን

የወሊድ ሐኪሞች፣ የመካንነት ሰብ-ስፔሻሊስቶችና የማህፀን ካንሰር ሰብ-ስፔሻሊስቶች።

የህፃናት

የህፃናት ሐኪሞችና ሰብ-ስፔሻሊስቶች — የህፃናት ነርቭ፣ ልብ፣ ሳንባ፣ ደምና የጨጓራ ሕክምና።

ቀዶ ሕክምና

አጠቃላይ፣ ላፓሮስኮፒክ፣ የነርቭ፣ የአከርካሪ፣ የአጥንት፣ የኩላሊትና ሽንት፣ የፕላስቲክና የደም ቧንቧ ቀዶ ሕክምና።

ሌሎች

የዓይን፣ የጆሮ አፍንጫ ጉሮሮ፣ የጥርስና የመንጋጋ፣ የቆዳ፣ የካንሰርና የአዕምሮ ሕክምና።

ቀጠሮ ለመያዝ

  1. ሐኪም ይምረጡ — በየሐኪሞች ገጽ ላይ በስም ወይም በሙያ ይፈልጉ።
  2. ቀጠሮ ይጠይቁ — በገጹ ላይ ያለውን ቅጽ ይሙሉ ወይም 9000 ይደውሉ።
  3. ማረጋገጫ — ከጥሪ ማዕከላችን ተደውሎ ቀኑና ሰዓቱ ይረጋገጣል።

የትኛውን ሐኪም ማየት እንዳለብዎ እርግጠኛ ካልሆኑ 9000 ይደውሉ — የጥሪ ማዕከላችን ወደ ትክክለኛው ክፍል ይመራዎታል።

ማስታወሻ

የሐኪሞች ዝርዝር ገጽ በእንግሊዝኛ ነው። በስም ወይም በሙያ መፈለግ ይችላሉ። እገዛ ከፈለጉ 9000 ወይም +251 935 402 078 ይደውሉ።