Generic selectors
Exact matches only
Search in title
Search in content
Post Type Selectors
English

ጠቢብ የምርመራ ማዕከል

ኤምአርአይ፣ ሲቲ ስካን፣ ዲጂታል ኤክስሬይ፣ አልትራሳውንድና ሰፊ የላብራቶሪ አገልግሎት በአንድ ቦታ። ከሌላ ተቋም በሪፈራል ለሚመጡ ታካሚዎችም ክፍት ነው።

የምንሰጣቸው ምርመራዎች

ኤምአርአይ (MRI)

ለአንጎል፣ ለአከርካሪ፣ ለመገጣጠሚያና ለሆድ ዕቃ ምርመራ። ጨረር የለውም።

ሲቲ ስካን (CT)

ለአደጋ፣ ለሳንባ፣ ለሆድ ዕቃና ለደም ቧንቧ ምርመራ። በፍጥነት ውጤት ይሰጣል።

ዲጂታል ኤክስሬይ

ለስብራት፣ ለሳንባና ለደረት ምርመራ።

አልትራሳውንድ

የሆድ ዕቃ፣ የፅንስ ክትትል፣ 4D አልትራሳውንድ እና በአልትራሳውንድ የሚመራ ናሙና መውሰድ።

የልብ ምርመራ

ኢኮካርዲዮግራፊ፣ ኢሲጂ፣ የ24 ሰዓት ሆልተር ክትትልና የጭንቀት ምርመራ።

DEXA — የአጥንት ጥንካሬ

የአጥንት መሳሳት (osteoporosis) ስብራት ከመድረሱ በፊት ለመለየት። ለሴቶች ከማረጥ በኋላ በተለይ ይመከራል።

ፋይብሮስካን

የጉበት ጥንካሬና ጠባሳ መጠን ያለ ናሙና መውሰድ (biopsy) ይለካል። ለሄፓታይተስና ለጉበት ስብ ሕመም።

ኢንዶስኮፒ

የጨጓራና የአንጀት ምርመራ፣ ኮሎኖስኮፒ፣ ERCP እና EUS።

ላብራቶሪ

መደበኛ ምርመራዎችና ልዩ ምርመራዎች — የሆርሞን፣ የበሽታ መከላከል ሥርዓት (autoimmune)፣ የመድኃኒት መጠን ክትትልና የቅድመ ወሊድ ምርመራ። አብዛኞቹ ውጤቶች በ24 ሰዓት ውስጥ።

ምርመራ ከማድረግዎ በፊት

  • የሐኪም ማዘዣ — ካለዎት ይዘው ይምጡ። ከሌለዎት የእኛ ሐኪሞች መርምረው ያዛሉ።
  • ጾም — ለአንዳንድ የደምና የሆድ ዕቃ ምርመራዎች ከ6 እስከ 8 ሰዓት መጾም ያስፈልጋል። ቀጠሮ ሲይዙ ይጠየቁ።
  • ለኤምአርአይ — በሰውነትዎ ውስጥ ብረት፣ pacemaker ወይም ሌላ መሣሪያ ካለ አስቀድመው ይንገሩን።
  • ለነፍሰ ጡር እናቶች — እርጉዝ መሆንዎን አስቀድመው ይግለጹ፤ አንዳንድ ምርመራዎች ጨረር ስላላቸው።
  • የቀድሞ ውጤቶች — ያለፈ ሲዲ፣ ፊልም ወይም ውጤት ካለዎት ይዘው ይምጡ፤ ለንጽጽር ይጠቅማል።

ውጤት መቼ ይደርሳል?

አብዛኞቹ የላብራቶሪ ውጤቶች በ24 ሰዓት ውስጥ፣ አንዳንድ የምስል ምርመራዎች በዚያው ቀን ይደርሳሉ። ለመረጃ 9000 ወይም +251 935 402 078 ይደውሉ።