Generic selectors
Exact matches only
Search in title
Search in content
Post Type Selectors
English

በአዲስ አበባ ሆስፒታል እንዴት መምረጥ ይቻላል

ብዙ ሰው ሆስፒታል የሚመርጠው ችግር ሲፈጠር፣ በችኮላ ነው። ከዚያ በፊት ማወቅ የሚገቡ ስድስት ጥያቄዎች፣ እና የእኛ መልስ።

ማንኛውንም ሆስፒታል ሊጠይቁ የሚገቡ ስድስት ጥያቄዎች

  1. በሌሊት ስፔሻሊስት በቦታው አለ ወይስ ይጠራል? ለልብ ድካም፣ ለአደጋ ወይም ለህፃን ድንገተኛ ሕመም ልዩነቱ በደቂቃ ይለካል።
  2. ሕመሙን ማከም ይችላል ወይስ ማወቅ ብቻ? ሲቲ ስካን ኖሮት የቀዶ ሕክምና ክፍል ወይም ካቴተር ላብራቶሪ የሌለው ሆስፒታል መልሶ ይልክዎታል።
  3. ይህን ሕክምና በዓመት ስንት ጊዜ ያደርጋሉ? ለውስብስብ ሕክምናዎች ልምድ ውጤትን ይወስናል። ቁጥሩን መጠየቅ መብትዎ ነው።
  4. የጽኑ ሕሙማን ክፍል (ICU) አለ? ቀዶ ሕክምና ደህና የሚሆነው ከሕክምናው በኋላ የሚሰጠው እንክብካቤ ሲኖር ነው።
  5. ላብራቶሪው በራሱ ይሰራል? ናሙና ወደ ውጭ የሚላክ ከሆነ ውጤቱ ቀናት ይፈጃል፤ ውሳኔው ግን ዛሬ ያስፈልጋል።
  6. ወጪው ስንት ነው? ኢንሹራንስ ምን ይሸፍናል? ግምቱን በጽሑፍ ይጠይቁ — አልጋ፣ የቀዶ ሕክምና ክፍል፣ ሐኪምና መድኃኒት ጨምሮ።

የእኛ መልስ

150አልጋዎች
12የቀዶ ሕክምና ክፍሎች
2,000+የኢንተርቬንሽናል ሕክምናዎች
170+ሐኪሞች

የድንገተኛ ክፍላችን በ24 ሰዓት ይሰራል፤ የህፃናት ቀዶ ሕክምና ባለሙያ በማንኛውም ሰዓት ይገኛል። የጽኑ ሕሙማን ክፍልና የህፃናት ጽኑ ሕሙማን ክፍል ሁልጊዜ በባለሙያ ይሸፈናሉ። ምርመራና ሕክምና በአንድ ሕንፃ ውስጥ ይከናወናሉ — ከኤምአርአይና ሲቲ ስካን እስከ ካቴተር ላብራቶሪ፣ የቀዶ ሕክምና ክፍሎች፣ ዲያሊሲስ፣ ኬሞቴራፒና IVF ድረስ።

ላብራቶሪያችን ልዩ ምርመራዎችን ጭምር በራሱ ይሰራል፤ አብዛኞቹ ውጤቶች በ24 ሰዓት ውስጥ ይደርሳሉ።

በኢትዮጵያ ቀዳሚ የሆንባቸው

በኢትዮጵያ የኢንዶስኮፒክ አልትራሳውንድ (EUS) አገልግሎትን በመጀመር የመጀመሪያው ሆስፒታል ነን፤ በ EUS የሚመሩ cystogastrostomy እና choledochoduodenostomy ሕክምናዎችንም በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አከናውነናል። በነሐሴ 2026 የ TAVI ሕክምና በቀጥታ ስርጭት ለአፍሪካ የልብ ሕክምና ባለሙያዎች ጉባኤ አስተላልፈናል። ክፍት የልብ ቀዶ ሕክምና በዝግጅት ላይ ነው።

ሌላ ሆስፒታል የሚሻልበት ጊዜ

ግልጽ እንሁን። የአካል ክፍል ንቅለ ተከላ (transplant) ወይም የጨረር ሕክምና (radiotherapy) አንሰጥም፤ ስለዚህ እነዚህ ካስፈለጉ ወደ ሌላ ተቋም እንልክዎታለን። እንደ ጥቁር አንበሳና ቅዱስ ጳውሎስ ያሉ የመንግሥት ሪፈራል ሆስፒታሎች የሚሰጧቸው አገልግሎቶችና የዋጋ ድጋፍ በግል ሆስፒታል አይገኙም። ለቀላል ሕመም ደግሞ በአቅራቢያዎ ያለ ክሊኒክ ፈጣንና ርካሽ ነው። እኛ የምንሰጠው ልዩ ምርመራና ሕክምና በአንድ ቦታ፣ ያለ ረጅም ወረፋ ነው።

የትኛው ክፍል እንደሚያስፈልግዎ እርግጠኛ ካልሆኑ

9000 ይደውሉ። የጥሪ ማዕከላችን ችግርዎን ሰምቶ ወደ ትክክለኛው ክፍል ይመራዎታል። ወይም ቀጠሮ ይያዙ።